3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ
የአይከን ሪል እስቴት አ.ማ. ባለአክስዮኖች 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ የጉባኤ ጥሪ በኢ.ፌ.ድ.ሪ ንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀፅ 366(1)፣ 367(1)፣ 370፣393(1) እና 400(1) እንዲሁም በአክስዮን ማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 23 መሠረት የአይከን ሪል እስቴት አክስዮን ማህበር 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እሁድ ታህሳስ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ በግራንድ ኤልያና ሆቴል ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም የተከበራችሁ የአክስዮን ማህበሩ ባለአክስዮኖች በዕለቱ በጉባኤው ላይ እንድትገኙልን የማህበሩ የዳይሬክቶሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
1) አክስዮን ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
1.1 የአክስዮን ማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ አዲስ አበባ ከተማ፣ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 06 ቤተል ከፖሰታ ቤት አጠገብ ዉብ ታወር 2ኛ ፎቅ
1.2 የማህበሩ የንግድ ምዝገባ ቁጥር አአ/2/0015904/2015
1.3 የንግድ ስራ ፈቃድ ቁጥር አአ/14/667/4483190/2015
1.4 የማህበሩ የተፈረመው ዋና ገንዘብ (ካፒታል) ብር 252,000,000.00
1.5 የተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል) ብር 252,000,000.00
2) የ3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
2.1 የድርጅቱን የአንድ አመት ስራ አፈፃፀም ሪፖርት ማዳመጥ እና መገምገም
2.2 የድርጅቱን የ2018 ዓመት ረቂቅ እቅድ ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ
2.3 የተቆጣጣሪ ቦርድ አባላትን አበል ክፍያ መወሰን
3) ማሳሰቢያ፡-
3.1 በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክስዮኖች ተወካዮች ህጋዊ የውክልና ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ወይም በንግድ ህጉ አንቀፅ 337 መሠረት ጉባኤው ከመካሄድ ከሦስት ቀን በፊት በዋናው መስሪያ ቤት 2ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ስራ አስፈፅሚ ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ ለዚሁ አላማ በማህበሩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅፅ ሞልተው በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባኤ ተካፋይ ለመሆንና ድምፅ ለመስጠት የሚችል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
3.2 ባለአክስዮኖቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ለመሳተፍ ሲመጡ የታደሰ መታወቂያ፣ የፋይዳ መታወቂያ፣ የፓስፖርት፣ መንጃ ፈቃድ ይዘው መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡
የአይከን ሪል እስቴት አ.ማ. የዳይሬክቶሮች ጉባኤ
